እሴይ መሰረታዊ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ኃላፊነቱ የተወሰነ በጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. (October 20, 2024) በ222 መስራች አባላት ተመስርቶ ወደ ስራ ገባ።
ማህበሩ የተመሰረተው የጋራ ፍላጎትና አላማ ያላቸውን ግለሰቦች በማስተባበር፣ በጋራ ትብብር ህልማቸውንና ምኞታቸውን እንዲያሳኩ ለመርዳት ነው።
እሴይ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በአዋጅ ቁጥር 985/2009 መሰረት የተመዘገበ ህጋዊ እውቅና ያለው ተቋም ነው። ማህበሩ ከኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም (November 25, 2024) በምዝገባ ቁጥር ECC/008/17 ይፋዊ የስራ ፍቃድ አግኝቷል።
ልዩ የሚያደርገን፦ እሴይ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲንቀሳቀስና ቅርንጫፎችን መክፈት እንዲችል ከኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ቀጥተኛ ማረጋገጫና ፍቃድ ያገኘ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የህብረት ስራ ማህበር ነው። ይህም በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ አባሎቻችን ተደራሽ እና ታማኝ አገልግሎት እንድንሰጥ ያስችለናል።
እኛ ለእኛ
- ጠንካራ የቁጠባ ባህልን ማሳደግ፦ ጠንካራ የቁጠባ ባህል ያለው ማህበረሰብ በመገንባት እና የአባሎቻችንን ቁጥር በማስፋት ተፅዕኖ ፈጣሪ ተቋም መገንባት።
- ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ቀልጣፋ አሰራር፦ ብቁ የሰው ኃይል እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለቁጠባ፣ ለብድር እና ለብድር መክፈያ የሚሆኑ ቀላል እና ቀልጣፋ አሰራሮችን መዘርጋት።
- ስጋቶችን መቀነስ እና ዘላቂ ፋይናንስ፦ ተደራሽ በሆኑ የማይክሮ-ኢንሹራንስ (አነስተኛ መድን) አገልግሎቶች አማካኝነት ስጋቶችን መቀነስ እና ለሁሉም አባሎቻችን ዘላቂ የፋይናንስ ምንጭ መኖሩን ማረጋገጥ።
'' በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ቁጥር አንድ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር መሆን። ''
ዋናው ግባችን ለአባሎቻችን እና ለአካባቢው ማህበረሰብ የፋይናንስ ትምህርትና ስልጠና በመስጠት ጠንካራ የቁጠባ ባህልን ማሳደግ ነው። ግለሰቦች ውጤታማ የገንዘብ አያያዝ እውቀት ኖሯቸው የኢኮኖሚ ፈተናዎቻቸውን በዘላቂነት እንዲፈቱ እና ማህበራዊ ትስስራቸውን እንዲያጠናክሩ ማስቻል እንፈልጋለን።
የአባልነት መስፈርቶች
ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱትን ምድቦች አጠቃላይ ዝቅተኛ ክፍያ በአንድ ላይ በመክፈል ወዲያውኑ የማህበሩ አባል መሆን ይችላሉ።
የእሴይ ማህበር አባል መሆን በርካታ የፋይናንስ እና ማህበራዊ ጥቅሞችን ያስገኝልዎታል፦