ስለ እኛ

እሴይ (Essey) የተመሰረተው በ2017 ዓ.ም (እ.ኤ.አ በ2024) ነው።

እሴይ መሰረታዊ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ኃላፊነቱ የተወሰነ በጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. (October 20, 2024) በ222 መስራች አባላት ተመስርቶ ወደ ስራ ገባ።

ማህበሩ የተመሰረተው የጋራ ፍላጎትና አላማ ያላቸውን ግለሰቦች በማስተባበር፣ በጋራ ትብብር ህልማቸውንና ምኞታቸውን እንዲያሳኩ ለመርዳት ነው።

እሴይ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በአዋጅ ቁጥር 985/2009 መሰረት የተመዘገበ ህጋዊ እውቅና ያለው ተቋም ነው። ማህበሩ ከኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም (November 25, 2024) በምዝገባ ቁጥር ECC/008/17 ይፋዊ የስራ ፍቃድ አግኝቷል።

ልዩ የሚያደርገን፦ እሴይ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲንቀሳቀስና ቅርንጫፎችን መክፈት እንዲችል ከኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ቀጥተኛ ማረጋገጫና ፍቃድ ያገኘ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የህብረት ስራ ማህበር ነው። ይህም በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ አባሎቻችን ተደራሽ እና ታማኝ አገልግሎት እንድንሰጥ ያስችለናል።

እኛ ለእኛ

ለተሻለ ነገ ዛሬውኑ ቁጠባ ይጀምሩ!

ስለ እኛ

ተልዕኳችን

- ጠንካራ የቁጠባ ባህልን ማሳደግ፦ ጠንካራ የቁጠባ ባህል ያለው ማህበረሰብ በመገንባት እና የአባሎቻችንን ቁጥር በማስፋት ተፅዕኖ ፈጣሪ ተቋም መገንባት።

- ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ቀልጣፋ አሰራር፦ ብቁ የሰው ኃይል እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለቁጠባ፣ ለብድር እና ለብድር መክፈያ የሚሆኑ ቀላል እና ቀልጣፋ አሰራሮችን መዘርጋት።

- ስጋቶችን መቀነስ እና ዘላቂ ፋይናንስ፦ ተደራሽ በሆኑ የማይክሮ-ኢንሹራንስ (አነስተኛ መድን) አገልግሎቶች አማካኝነት ስጋቶችን መቀነስ እና ለሁሉም አባሎቻችን ዘላቂ የፋይናንስ ምንጭ መኖሩን ማረጋገጥ።

ራዕያችን

'' በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ቁጥር አንድ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር መሆን። ''

ግቦቻችን

ዋናው ግባችን ለአባሎቻችን እና ለአካባቢው ማህበረሰብ የፋይናንስ ትምህርትና ስልጠና በመስጠት ጠንካራ የቁጠባ ባህልን ማሳደግ ነው። ግለሰቦች ውጤታማ የገንዘብ አያያዝ እውቀት ኖሯቸው የኢኮኖሚ ፈተናዎቻቸውን በዘላቂነት እንዲፈቱ እና ማህበራዊ ትስስራቸውን እንዲያጠናክሩ ማስቻል እንፈልጋለን።

እሴቶቻችን

  • - ራስን መርዳት እና በራስ መተማመን
  • - ተጠያቂነት እና የደንበኛ ክብር
  • - ዲሞክራሲያዊ ባህል እና የሕግ የበላይነት
  • - እኩልነት
  • - ፍትሃዊነት እና ርትዕ
  • - አንድነት እና ወንድማማችነት

አባልነት

የአባልነት መስፈርቶች

  1. ማንነትን የሚገልፅ፦ የታደሰ ብሔራዊ መታወቂያ ኮፒ እና 2 የፓስፖርት መጠን (Passport-sized) ፎቶግራፎች።
  2. የእሴት/ዕጣ ክፍያ፦ ዝቅተኛውን የዕጣ ክፍያ (ካፒታል) የመክፈል አቅም።
  3. የወርሃዊ ቁጠባ፦ ዝቅተኛውን የወርሃዊ ቁጠባ መጠን በየወሩ ለመቆጠብ ፈቃደኛ መሆን።
  4. የአገልግሎት ክፍያ፦ የተደነገገውን የመመዝገቢያ ወይም የአገልግሎት ክፍያ መክፈል።

ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱትን ምድቦች አጠቃላይ ዝቅተኛ ክፍያ በአንድ ላይ በመክፈል ወዲያውኑ የማህበሩ አባል መሆን ይችላሉ።

የአባልነት ጥቅሞች

የእሴይ ማህበር አባል መሆን በርካታ የፋይናንስ እና ማህበራዊ ጥቅሞችን ያስገኝልዎታል፦

  • ዓመታዊ የትርፍ ክፍፍል፦ ከማህበሩ ዓመታዊ ትርፍ ላይ የእርስዎን ድርሻ (ዲቪደንድ) ያግኙ።
  • ከፍተኛ የወለድ ክፍያ፦ ለሚያስቀምጡት ቁጠባ አስተማማኝ እና ከፍተኛ የቁጠባ ወለድ ተጠቃሚ ይሁኑ።
  • አነስተኛ የወለድ ብድር ፦ ቀላል እና ወለዳቸው አነስተኛ የሆኑ የተለያዩ የብድር አገልግሎቶችን ያግኙ።
  • ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ፦ በማህበሩ ውሳኔዎች ላይ የመምረጥ እና በዕጩነት የመቅረብ (የመመረጥ) ሙሉ መብት ይኖርዎታል።
  • የሀብት ግንባታ፦ አስተማማኝ የወደፊት ህይወትን ለመገንባት የሚያስችል የረጅም ጊዜ የፋይናንስ ዋስትና ይፍጠሩ።
  • ነጻ ስልጠና እና ምክር፦ ከፍተኛ ጥራት ያለው የፋይናንስ አያያዝ ስልጠና እና የቢዝነስ ምክር አገልግሎቶችን ያለምንም ክፍያ (በነጻ) ያግኙ።

Professional Team

ስለ እኛ

Our Story

አገልግሎቶቻችን

ቁጠባ

ብድር

የማማከር አገልግሎት

© 2026 Essey Saving and Credit Coop. L.TD